“Be the change you want to see in the world.”

አሻራዬ መነቃቂያ ገፅ

“Be the change you want to see in the world.”

አሻራዬ መነቃቂያ ገፅ

እንደ ጨው ያለች ትንሽዬ ቅናት

(በሚስጥረ አደራው) ከአበባው መልኩ ግጥሞች ውስጥ “ቅናት” የተሰኘውን ሲበዛ እወደዋለሁ። በተለምዶ በሚወዱት ሰው መቅናት የፍቅር ምልክት ነው ይላሉ፤ የሌላው አይነት ቅናት(ምቀኝነት) መጥፎነቱ ጥያቄ ውስጥ ስለማይገባ አናነሳውም። የፍቅር ጥልቀቱ ባሳደገው የቅናት መጠን እንደሚገለጽ የምናምን ሰዎች አለን፤ ትክክል ነው ማለት ግን አይደለም። መቅናት የሚወዱትን የግል ከማድረግ የሚመነጭ ሃይል እንደሆነ በማሰብ የሚያደርሰውን...

ሲያምኑኝ ከፋኝ

(በሚስጥረ አደራው)  በእርግጥ…..ስስቅ አይተውኛል፤ በደስታ ስቦርቅ ስጮህ ሰምተውኛል። ሀዘንና ጭንቀት ይጋባል ስላሉኝ፤ በሽታዬን ለሌላው እንዳላጋባ፤ የውስጤን ደብቄ ደስተኛ መስዬ መታየት ጀመርኩኝ። የማስመስለው ደስተኛ መስዬ በመታየት የሰዎችን ክብር እንዳገኝ አልነበረም፤ የማስመስለው በእኔ ሀዘንና ጭንቀት ሌሎች እንዳይጨነቁ በማሰብ ብቻ እንጂ። ከዚህ በላይ ለሌሎች የሚሰጥ ምን ስጦታ አለ? የእናትነትን ፍቅር...

በመተው….

(በሚስጥረ አደራው) በቀደም ለታ አንዲት የማደንቃት ድምጻዊት ቃለመጠየቅ ሲደረግላት እየሰማሁኝ ነበር። ይህች ምርጥ ኢትዮጵያዊ ድምጻዊት ባለትዳር ነበረችና ጋዜጠኛው የሚከተለውን ጥያቄ ሰነዘረ። “በዚህ ሙያሽ ላይ ባለቤትሽ እርዳታ ያደርጋል? ይደግፍሻል?” “ባለቤቴ ይደግፈኛል……በመተው ይደግፈኛል፤ እራሴን እንድሆን በመተው፤ የስራ ቀጠናዬ ውስጥ ባለመግባት በመተው ይደግፈኛል” ብላ መለሰች። መልሷ ውስጤ...
ማኑዋል- Life’s Instruction Manual

ማኑዋል- Life’s Instruction Manual

(ሚስጥረ አደራው) ብዙ እቃዎችን ስንገዛ አብሮ የሚሰጠን የመመሪያ ደብተር ወይም ማንዋል አለ። ይህ ማኑዋል የገዛነው እቃ እንዴት እንደሚሰራ፤ እንዴት እንደሚገጣጠም፤ እንዴት እንደሚለወጥ፤ ችግር ካለ ማንን እንደምናማክር፤  ሌሎች ብዙ ስለ እቃችን ጠቃሚ እውነታዎችን የሚይዝ ደብተር ነው። ብዙዎቻችን ግን ይህንን ማኑዋል ጊዜ ወስደን አናነበውም። ማኑዋሉን ሳያነብ የገዛውን እቃ ለመገጣጥም የሚሞክር ሰው ምናልባት...

ምናልባት….ምናልባት…..

(በሚስጥረ አደራው) ቁርሴን ከረፈደ ስለበላሁኝ፤ የምሳ ሰዓቴን ለእረፍት ልጠቀምበት አሰብኩኝና፤ ከመስራ ቤቴ ፊት ለፊት ወዳለው መናፈሻ ሄድኩኝ። አግድም አግድም ከተዘረጉት ወንበሮች ወደ አንደኛው እየተጓዝኩኝ ሳለ፤ከሳሩ መካከል የቀደበቀች የወረቀት ቁራጭ አይኔን ሳበችኝ። በእጅ ጽሁፍ ከተጻፈ ደብዳቤ ላይ ተቀዳ የቀረች የወረቀት ቅዳጅ ናት። የወደቀ ወረቀት የማንሳት ልምድ ባይኖረኝም የሆነ ስሜት ይህቺን የወረቀት ቅዳጅ...