አለምን እየመራት ያለው ሰይጣን ማን ነው?

Posted on Posted in መነቃቂያ

(በሚስጥረ አደራው)

“ወደድንም ጠላንም ህይወታችን ለፈጣሪ ባለን የምስጋና መጠን ይወሰናል። ህይወታችንን እጅግ መልካም ለማድረግ አልያም እርግማን ወደሞልው የሰቀቀን ኑሮ ለመለወጥ የሚያስችለን የገዛ አመለካከታችን ነው። አንዳንዶቻችን በቤታችን ጓሮ የተተከለውን ጽጌሬዳ ስንመለከት ጽጌሬዳው በእሾህ መወረሱ ያበሳጨናል፤አንዳንዶች ደግሞ እሾሁ ጽጌሬዳ ማብቀሉ ይገርማቸዋል። ሁሉ ነገር እኛ በሚኖረን የህይወት መነጽር ይወሰናል።

ወደ ዘላለማዊነት ከመሸጋገራችን በፊት የሚኖረን ብቸኛ ህይወት ይሄ ነው። በዚህች አንድ ጊዜ በምንኖራት ህይወት ደስተኛ መሆንን ከመረጥን ዋነኛው መንገድ ማመስገን መቻል ነው። ትንሽ በሆነው ነገር ማመስገን የሚችል ሰው በትልቁ የሚደሰት ነው። የማታመሰግን ነፍስ ግን ዘወትር የተማረረችና ደስታ የጎደላታ ናት።

የሚገርመው የገዛ አንደበታችን ወደ ደስተኛነት ወይም ወደ መራራ ኑሮ የሚያስገባን ድልድይ መሆኑ ነው። አንዳንዴ ሰዎች ወደኔ ይመጡና “አለማችንን እየመራት ያለው ሰይጣን ማነው?” ብለው ይጠይቁኛል። መልሴ “ከገሃነም የተባረረው መልዓክ ነው” የሚለው እንዲሆን ይጠብቃሉ፤ እኔ ግን እውነቱን እንዲህ ስል እነግራቸዋለው “አለማችንን የሚመራት ሃይለኛው ሰይጣን “ምስጋናቢስነት” ነው እላቸዋለሁ።

ምስጋናቢስነት የሚያመጣውን ችግር እና መከራ አትናቁት። ሰዎች ሃዘን የተሞላው ኑሮ እንዲኖሩ የሚያስገድዳቸው በአለም የሰፈነው ምስጋናቢስነት እና አብዝቶ ከማማረር የሚመነጨው ክፋት መሆኑን አትርሱ። ስላለን ነገር ማመስገን የጀመርን እለት እንደገና እንደተወለድን ይቆጠራል። ህይወት እንኳን  ሳያመሰግኗት እያማረሯት ይቅርና እንዳውስ ሞልታ ትሞላልች?”- ይህንን የተናገረው ፍራሲስ ፍራግቴን የተባለ የሃይማኖት ጸሃፊ የፈረንጆቹን የምስጋና በዓል አስመልክቶ በጻፈው አጭር መልዕክት ላይ ነው።

አመስጋኝ መሆን ትልቅ የመንፈስ ጥልቀትን ይጠይቃል። ነገሮች እንዳሰብናቸው ሳይሆኑ ቀርተው ተመስገን እያልን ነገን መናፈቁ ቀላል አይደለም፤ ትልቅ የመንፈስ ጥንካሬን ይጠይቃል። እንደውም በቅርቡ የተመለከትኩት የፕሮፌሰር ሃይሌ ገሪማ “ጤዛ” የተሰኘው ፊልም ላይ  አንዷ መከራ ያጎበጣን ገጸባህሪ በእንጉርጉሮዋ የተቀኘችው ትዝ አለኝ (የህዝብ ግጥም ይመስለኛል)

“አምላኬን አግኝቼ ምነው በነገርኩት

የደላኝ መሰለው ተመስገን ስላልኩት”

አንጀት የሚበላ ስንኝ አይደለም? በማመስገኗ ፈጣሪዋ ደልቷታል ብሎ እንዳይተዋት የፈራች ይመስላል። አንዳንድ ሰዎች ስለደላቸውና ሁሉ ስለሞላላቸው አይደለም የሚያመሰግኑት፤ በማማረር ምንም መፍትሄ ማግኘት እንደማይችሉ ስለገባቸው ብቻ እንጂ። ነገር ግን አንዳንዴ በሰው የሚደረሰውን መከራ ስናይ “አታመሰግንም” ብሎ መውቀሱ ትንሽ የሚከብ ይመስለኛል። (አንድ ቀልደኛ አዎንታዊ አስተሳሰብ የሁሉ ነገር መፍትሄ ነው የሚባለውን ሃሳብ ሲተች እንዲህ ብሎ ነበር “አዎንታዊ አስተሳሰብ ( Positive thinking and Law of attraction) ለራበው አንድ የአፍሪካ ህጻን መፍትሄ አይሆንም፤ ዳቦን በአይምሮ ስለሳለ ብቻ ጠግቦ አያድርም” ሲል ቀልዷል ) እንደቀልድ ይናገረው እንጂ እውነታ አለው፤ ብዙ የአልም ህጎች እውነታ ይፈትናቸዋል። ይህ እኔንም ሁሌ ግራ የሚያጋባኝ የህይወት ተቃርኖ ነው።

ወደተነሳንበት ሃሳብ ስንመለስ ግን ለተደረገልን መልካም ነገር ሁሉ ማመስገኑ ደግ ነው፤ ምንም ያህል ጥቂት ቢመስልም እንኳን። ለፈጣሪም ለሰውም ምስጋናቢስ መሆን በምንም መንገድ ደስታና በረከትን አይጨምርም። ለማመስገን የሚያስችን አንድ ነገር መቼም ከህይወታችን አናጣምና። ይህች አንዲት መስጋና ደግሞ ሌሎች መልካም ነገሮችን ትጎትታለች።

4 thoughts on “አለምን እየመራት ያለው ሰይጣን ማን ነው?

 1. Dear
  thanks for everything.behulu amesegenu new yemelew teleku metsehaf balene neger becha sayehon belelenem neger mamesegenen yemesel telek neger yelem.anchim endaleshew beteneshui mamesegen yalechal endet beteleku neger liyamesegn yecheal lezehem new bezu neger beafe yemetal.yechen tekese eski anebebiyat badom honom sew yamesegenal yelal
  17 ምንም እንኳ በለስም ባታፈራ፥ በወይንም ሐረግ ፍሬ ባይገኝ፥ የወይራ ሥራ ቢጐድል፥ እርሾችም መብልን ባይሰጡ፥ በጎች ከበረቱ ቢጠፉ፥ ላሞችም በጋጡ ውስጥ ባይገኙ፥

  18 እኔ ግን በእግዚአብሔር ደስ ይለኛል በመድኃኒቴ አምላክ ሐሤት አደርጋለሁ።Tnebet Enbakom 3:17-18
  thanks
  Aereham

Do you have any comments?