“Be the change you want to see in the world.”

አሻራዬ መነቃቂያ ገፅ

“Be the change you want to see in the world.”

አሻራዬ መነቃቂያ ገፅ

ባዶነትና ደስ የሚለው ዜማ

(በሚስጥረ አደራው) “listened to the story told by reed of being separated since i was cut from the reedbed i have made this crying sound” -Rumi መቃው ሲናገር ስሙ፤ በዜማው ሲጮኸው ብሶቱን ናፍቆቱን ሲያስተጋባ፤ ቁልቁል ሲናፍቅ መሬቱን የጠቢባን ሁሉ ዜማ፤ የጥበብ ጩኸት በራሱ ናፍቆት ነው መነሻው፤ ባዶነት ነው ጥንስሱ እንደ ሩሚ...

ልምጥነት The beauty of Flexiblity

(በሚስጥረ አደራው) ልምጥነት ለ Flexiblity ያገኘሁት ተቀራራቢ ቃል ነው። ስለዚህ በዚህ ጽሁፍ ልምጥነት ስል Flexiblityን እየገለጽኩ እንደሆነ ይታወቅልኝ። ግትርነት ከሰው እስከ ህይወት የሚያነካካን መልካም ያልሆነ ባህሪ ነው። ነገሮች እኛ ባላሰብናቸው መንገድ ሳይሄዱ ሲቀሩ ፤ ከህይወት ጋር እንዴት ነው መግባባት የምንችለው? እንዴት ነው እጥፍ ዘርጋ ብለን ከኑሮ ንፋስ ጋር መሄድ የምንችለው? ለዚህ ጽሁፍ ሶስት...

ህልምህን እየገደልከው ነው? Are You killing your Dreams?

(በሚስጥረ አደራው) ህልም እስከወዲያኛው ይሞታል ብዬ አላምንም። ነገር ግን ይቀበራል። ሳይሞት የሚቀበር ነገር ህልም ነው። የሰው ልጅ ያለ ህልም አይኖርም፤ አዲስ ጫማ ከመግዛት አንስቶ ሌላ ሰው እስከመሆን ድረስ ያልማል። አንዳንዴ ህልሙ እውን ሆኖለት የፈለገውን ሲያገኝ፤ ሌላ ጊዜ ደግሞ ህልሙን በምክንያት ቀብሮ የኑሮ ጉዞውን ይቀጥላል። ህልም ሳይሞት ይቀበራል ያልኩት፤ ሰው በውስጡ “እንዲህ ማድረግ እኮ እፈልግ...

ሰኞ ለት ተያየን በድንገት…..እሁድ ቅልጥ ያለው መውደድ

(በሚስጥረ አደራው) “ሰኞ ለት ተያየን በድንገት ማክሰኞ በህልሜ መጣ ሞኞ እሮብን ለፍቅር ተሳሰብን ሀሙስ ልቤን አለው ደስ ደስ አርብ ላይ ብንውል ሳንተያይ ቅዳሜ ተኛሁኝ ታምሜ እሁድ ቅልጥ ያለው መውደድ” ሰኞ ተጠንስሶ እሁድ ከፍጻሜ የደረሰ ፍቅር አጋጣሟችሁ ያውቃል? ፍቅር እንዲህ መንገዱ አልጋ በአልጋ ቢሆን ማን ይጠላ ነበር። ሰኞ ያገኙትን ሰው እሮብ ለፍቅር ማሰብ፤ ሀሙስ በደስታ መጥለቅለቅ፤ አርብ...