“Be the change you want to see in the world.”

አሻራዬ መነቃቂያ ገፅ

“Be the change you want to see in the world.”

አሻራዬ መነቃቂያ ገፅ

በፍቅርና በሐይማኖት ስም…….

(በሚስጥረ አደራው) ለዚህ አጭር ጽሁፍ ሁለት አባባሎችን በአንድ ላይ ልጠቀም እፈልጋለው። እውቁ የመንፈሳዊ መምህር ዳይላ ላማ፤ ስለፍቅር እና ስለ ሐይማኖት በተለያዩ ግዜያት የተናገሯቸውን ድንቅ አባባሎች ነው ልጠቀም የሻትኩት። “ለምትወደው ሰው የሚበርበትን ክንፍ፤ ተመልሶ የሚመጣበትን ስር፤ ካንተ ጋር የሚቆይበትን ምክንያት ስጠው” ብለዋል። በሌላ ንግግራቸው ደግሞ ስለሀይማኖት እንዲህ ሲሉ ተናግረዋል፤ “የሀይማኖት አላማ...

ጸንተህ ለመቆም ከፍርሃትህ የሚበልጥ ነገር ፈልግ!

ፍርሃት በሁለት መንገድ የሚከፈል ይመስለኛል። አንደኛ እራሳችን የምንፈጥረው ፍርሃት ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ሌሎች በውስጣችን የሚጭሩት ፍርሃት ነው። ሁለቱም ሀይለኛ ስሜቶች ናቸው። ሁለቱም ጉልበትን የማሸብረክ፤ ውሳኔን የማስቀየር፤ አላማን የማሳት፤ አሸማቆ ወደ ብቸኝነት ጉድጓድ የማስገባት ጉልበት አላቸው። እራሳችን በራሳችን የምንፈጥረውና ሌሎች በኛ ሊጭሩት የሚሞክሩት ፍርሃት የየራሳቸው ባህሪ አላቸው። እንደሚከተለው...

ዝምታ መልስ ይሆናል?

“ለዋልኩት ውለታ ይሄነው ወይ ውርሴ? ልፋቴ ድካሜ ይሄ ነው ወይ ውርሴ? እንግዲህ ምን ልበል ይህ ከሆነ ቅርሴ አሃ….ዝምታ ነው መልሴ ክፉ ደግ አትበል አታውጋ ምላሴ አሃ ዝምታ ነው መልሴ…….” ማዳመጫዬን ሰክቼ የማዳምጠው ይህንን ውብ የመሐሙድን የሀዘን ድባብ የተላበሰ ዘፈን ነበር። እውነት ግን ዝምታ ትክክለኛ መልስ ይሆናል? ሰው መልካም ስራ ሰርቶ የማይገባውን ክፍያ...

መጀመሪያ ቃል ነበረ……

“መጀመሪያ ቃል ነበረ….” ይላል ቅዱሱ መጽሃፍ። ቃል ትልቅ ሀይል እና ጉልበት ያለው ነገር መሆኑን ይህ ጥቅስ ያስረዳል። ይህ አባባል ከሀይማኖታዊ ትርጓሜው በዘለለ በእለት ተእለት ኑሮዋችንም ትልቅ ጉልበት ያለው መልዕክት ነው። በቃል መልካምም መጥፎም ነገሮች በኑሮዋችን ውስጥ ህይወት ይዘራሉ። እውን ሆነው በአይናችን የምናያቸው ነገሮች ሁሉም ሁለቴ የተፈጠሩ ናቸው። በመጀመሪያ በአይምሮዋችን...