“Be the change you want to see in the world.”

አሻራዬ መነቃቂያ ገፅ

“Be the change you want to see in the world.”

አሻራዬ መነቃቂያ ገፅ

የሚያንጠባጥበው ቀረጢት

(በሚስጥረ አደራው) ይህችንን ተረት ድንገት ሰማኋትና የሳምንቱ መነቃቂያ ትሆነን ዘንድ መረጥኳት። በአንድ መንደር የሚኖር አንድ ልጅ ነበር ። ይህ ልጅ በጣም ውድ የሆኑና ከባህር ውስጥ የሚገኙ ብዙ ድንጋዮኝ ነበሩት። ታዲያ እኒህን ውድ ድንጋዮች በቀረጢቱ አድርጎ በየሄደበት ቀረጢቱን ይዞ ይጓዝ ነበር። ልጁ ስለነዚህ ድንጋዮች ብዙ ያስባል፤ ነገር ግን ከማሰቡ እና ከመንሰፍሰፉ በቀር ከቀረጢቱ አውጥቶ አይጫወትባቸውም ወይም...

ብቸኝነት እንዲሰማን የሚያደርጉን የገዛ ሚስጥሮቻችን ቢሆኑስ?

 በሚስጥረ አደራው የየለት ኑሮዋችንን  ጸሃይ ይሙቀው ማለት አንችልም። የምናስበውንና የምናደርገውን ለአላፊ አግዳሚው ማውራትም አይገባንም። ነገር ግን በውስጣችን ብዙ ሚስጥሮችን በያዝን ቁጥር፤ ከማን እንደምንሸሽ ባናውቅም ሁሌም እንደሸሸን ነው። ከልብ የሆኑና ስር የሚሰዱ ግንኙነቶችን መመስረት የሚሳነን በውስጣችን ብዙ የተቆለፈባቸው እውነታዎች ሲኖሩ ነው። በኑሮዋችን ውስጥ ለጭንቀት የሚዳርጉን፤ በየሄድንበት እንዲቆረቁሩን...

በአባቴ ምክንያት ቆሜ እንዳልቀር ፈራው

በሚስጥረ አደራው በአባቴ ምክንያት ቆሜ እንዳልቀር እፈራለው። እንዲህ ብዬ ወሬዬን ስጀምር የማታውቁትን አባቴን በክፉ አይናችሁ እንዳታዩብኝ እሰጋለው። ቆሜ የምቀረው አባቴ ምርጫዬን ስላልወደደልኝ አይደለም፤ ወይም እሱ የመረጠልኝን ስላላገባው። ለሱ ሰው ሁሉ መልካም እስከሆነ ድረስ እኩል ነው። ወላጆቼ በአንድ ጎጆ ኑሮዋቸውን ሀ ብለው ከጀመሩ እነሆ ግማሽ ምዕተ ዓመት ሊሆናቸው ነው። እርግጥ ነው በእኛ በኢትዪጵያን ዘንድ ይህ...

ሶስቱ አለሞች

በሚስጥረ አደራው የምን ሶስት አለም አመጣሽ ትሉኝ ይሆናል? ሶስቱ አለሞች ከውልደት በፊት፤ በምድር ላይና ከሞት በኋላ የምንኖርባቸው አለሞች አይደሉም። ሶስቱም አለሞች በህይወት እያለን የምንኖርባቸው አለሞች ናቸው። በእያንዳንዱ አለም ውስጥ የተለያየ  ኑሮ፤ የተለያዩ ስሜቶች፤ ይንጸባረቃሉ። አለሞቻችን መለያየታቸው መልካም ነገር ሆኖ ሳለ፤ ያንዱን አለም ኑሮ ከሌላው አለም ጋር ከደባለቅነው ግን ችግር ይፈጠራል። አንደኛው...

የፓንዶራ ሳጥን

በሚስጥረ አደራው ሰው በተስፋ ይኖራል ይባላል፤የአለምን ውጣ ውረድ የህይወትን ፈተና ሰው ማለፍ የሚችለው ተስፋ መቀነን ሲችል ብቻ ነው፤ዕውቁ ኢትዮጵያዊ ባለቅኔ ሎሬት ፀጋዬ ገ/ መድህን እንዲህ ሲል ሰው በተስፋ ይኖራል ይለናል። “ተስፋ መቀነን ነው መቼም የሰው ልጅ አይችለው የለም” ጭንቀት እና ውጥረት በማይለያት በዚህች አለም፤እራስን ማዳን የሚቻለው ተስፋ ሲኖረን ብቻ ነው።ተስፋ መቁረጥ በቁም ከመሞት እንዳማይለይ እርግጥ...