“Be the change you want to see in the world.”

አሻራዬ መነቃቂያ ገፅ

“Be the change you want to see in the world.”

አሻራዬ መነቃቂያ ገፅ

የወርቅ እንቁላሎች

በየጊዜው በምንጸልየው ጸሎት ውስጥ  “የእዮብን ትዕግስት ስጠኝ” የምንለው የዚህችን ምድር ሰማይ ጠቀስ ፎቅ መወጣጫው ትዕግስት  ስለሆነ ነው። ትዕግስት ማለት ነገሮች በጊዜያቸው እንዲሆኑ መጠበቅ ቢሆንም፤ ከምንም በላይ ትክክለኛው ትዕግስት በጥበቃችን ወቅት የምናሳየው አመለካከት እና ጽናት ጭምር ነው። እዚህ ላይ ኤዞፕ የጻፈው አንድ ተረት ትዝ አለኝ። ተረቱ እንዲህ ነው……. በድሮ ጊዜ...

የሚያሳስበን ችግሩ ሳይሆን ችግሩን የምናይበት መንገድ ቢሆንስ?

(በሚስጥረ አደራው) ምንም እንኳን ስለመልካም አስተሳሰብ እና ስለ ቀና ኑሮ ደጋግመን ብንደሰኩርም አንድ መዋጥ ያለብን እውነት ግን አለ። ይህም ህይወት ነጭ እና ጥቁር አይደለችም። የጠበቅናቸው የማይከሰቱባት ያልጠበቅናቸው የሚከሰቱባት የማትተነበይ እንጂ። ችግር የማይደርስበት ኑሮ፤ ከመከራ ከሃዘን የራቀ ህይወት ለማንም አልተሰጠም። ማንም ሰው ሁሉ ተሳክቶለት እና ሞልቶለት የሚኖር አይኖርም (ምንም እንኳን ከላይ በምናያቸው...