by Mistre | Oct 27, 2015 | መነቃቂያ inspiring stories
ወቀሳ ለማንም ጠንካራ ነኝ ለሚል ሰውም ከባድ ሸክም ነው። ሌሎች ሲወቅሱን፤ ከጥፋታችን በላይ ሊቀጡን ሲሞክሩ ምን ይሰማናል? ወቀሳ እረፍት የሚነሳ፤ የሚያሸማቅቅ፤ ዝቅተኝነት እንዲሰማን የሚያደርግ ስሜት ነው። የሚገርመው ብዙን ጊዜ ከሌሎች ሰዎች ዘንድ የሚመጣውን ወቀሳ ነው እንጂ፤ እኛ በገዛ እራሳችን ላይ የምናዘንበውን ወቀሳ አስተውለነው አናውቅም። ሃዘናችን በብዛት የሚመነጨው እራሳችንን ይቅር ካለማለት ነው።...
by Mistre | Oct 20, 2015 | Guest writer-እንግዳ ጸሃፍት
“አፋዊ ሆንን፤ ሕያዊ ሳንሆን አፍአዊ ፤ ቃለ ህይወት ሳንሆን ብኩን ቃል-አፍ ብቻ! እንጂ ቤታችን አንድ ነው”- ከሎሬት ጸጋዬ ገ/መድህን “እናት አለም ጠኑ” ከተሰኘው ተውኔት የተወሰደ ` ቋንቋ እውነት መግባቢያ ነው! ነገር ግን ብቸኛው መግባቢያ እንዳልሆነ እርግጥ ነው። ይህንን ያስባለኝ ዛሬ አመሻሹ ላይ ያጋጠመኝ ነገር ነው። ሁሌም የኑሮ ልዩ ትርጉሞች፤ ተራ በሚመስሉ ነገሮች...
by Mistre | Oct 1, 2015 | መነቃቂያ inspiring stories
እራሱን መጣል የሚፈልግ ሰው የለም። ሁላችንም እራሳችንን ለመጠበቅ የተቻለንን እናደርጋለን። ንጹህ ለመልበስ፤ ውበታችንን ለማቆየት፤ የምንበላውን ለማዘጋጀት፤ የለንም ከምንለው ጊዜ እንደምንም ብለን ለመሻማት እንሞክራለን። ለውጫዊ ማንነታችን የተቻለንን ጊዜ፤ የተቻለንን ገንዘብ መስዋት እናደርጋለን። ችግሩ ግን የህይወታችን መሰረቱ የውጫዊ ማንነታችን አለመሆኑ ነው። ትልቁን አትኩሮት እና እንክብካቤ የሚሻው ውጫዊው አካላችን...
Recent Comments