“Be the change you want to see in the world.”

አሻራዬ መነቃቂያ ገፅ

“Be the change you want to see in the world.”

አሻራዬ መነቃቂያ ገፅ

ከአፍ የወጣ……..

በቀን ምን ያህል ክፉ ንግግሮችን እንናገር ይሆን? ምን ያህል መልካም ያልሆኑ ሃሳቦች አይምሮዋችንን  ሽው ይሉት ይሆን? መቼም አሁን በተያያዝነው የአኗኗዋር ዘይቤ……አስተሳሰባችን፤አነጋገረራችን፤አስተያየታችን ግራውን መከተሉን ለምዷል።ከራሳችን፤ከቤተሰቦቻችን፤ከጓደኞቻችን ጋር የምንጋጭበት ጊዜ ብዙ ነው።ከህጉ ጋር፤ከማህበረሰቡ ጋር፤ከእምነቱ ጋር የምንላተምበት አጋጣሚዎች ጥቂት የሚባሉ አይደሉም።አኗኗራችን  አስተሳሰባችንን...

መሶብ ሰፍቼ፤ ላም ገዝቼ…..

ይህንን ታሪክ ከልጅነቴ ጀምሮ፤ ከእናቴ አባቴ አፍ ሲቀባበል የሰማሁት ታሪክ ነው። በቤተሰባችን መሃከል ከዛሬ የራቀ ነገር ተነስቶ ክርክር ሲነሳ የአባቴ ወይም የእናቴ ማሳረጊያ ይህ ነው “መሶፍ ሰፍቼ….” እያሉ ታሪኩን ከዚህ በፊት አንድ ሺህ ጊዜ ደግመው ቢናገሩት እንኳን ደግመው ይተርኩታል። ታሪኩ ለፈገግታ በየመሃሉ ጣል የሚደረግ ቢመስልም፤ ሶስተኛ አይን ኖሮት ላስተዋለው ሰው ትልቅ መልዕክት...

በሰው ተስፋ አትቁረጥ

“You must not lose faith in humanity. Humanity is an ocean; if a few drops of the ocean are dirty, the ocean does not become dirty”–Mahtama Gandih ምናልባት ሰዎች በድለውህ፤ አልያም አስከፍተውህ ሊሆን ይችላል። ማን ያውቃል ያመንከው ከድቶህ፤ የጠበቅከው እረስቶህ፤ ተስፋ የጣልክበት ጥሎህ ሊሆንም ይችላል። ወይም...

እንዴት መታወስ ትፈልጋለህ?

አንድ ጊዜ አንድ ሰው የጠዋቱን ጋዜጣ ሲያነብ፤ በስህተት የወጣ አንድ አስደንጋጭ ዜናን ይመለከታል። ዜናው ስለራሱ የተዘገበ ነበር። ዘጋቢዎቹ በስህተት የወንድሙን ሞት እሱ እንደሞተ አድርገው ነበር የዘገቡት። የዜናው አርስትም  “የድማሚቱ ንጉስ አረፈ” ይልና “ይህ ሰው የሞት ነጋዴ ነበር” ሲል ያትታል። ይህ ሰው የዳናማይት (ድማሚት) ፈጣሪ አልፍሬድ ኖቤል ነበር። ወንድሙ ሲሞት እሱ...

ብቸኛዋ ፍቅር

አንድ ጊዜ የሰው ልጅ ስሜቶች ሁሉ ተሰብስበው ለሽርሽር ወደ አንድ ደሴት ይሄዳሉ። እንደየባህሪያቸው ሁሉም መልካም ጊዜን እያሳለፉ ነበር። ድንገት ግን ሃይለኛ ማዕበል ተነሶቶ ደስታቸውን አደፈረሰባቸው። ቶሎ ብለውም ደሴቱን መልቀቅ እንዳለባቸው አዋጅ ተላለፈ።  እያንዳንዳቸውም ስራቸውን አቋርጠው ወደየ ጀልባቸው እሩጫ ጀመሩ። ሁሉም ስሜቶች እራሳቸውን ለማዳን ሲሮጡ፤ ፍቅር ግን ቶሎ ለመሸሽ አልፈለግችም ነበር። ብዙ የምትሰራው...