“Be the change you want to see in the world.”

አሻራዬ መነቃቂያ ገፅ

“Be the change you want to see in the world.”

አሻራዬ መነቃቂያ ገፅ

መምህር ውሃ!!!

ከሰውነታችን 70 በመቶ ያህሉ ውሃ ነው። የእኛ ሰውነት ብቻም ሳይሆን የምድርም ተመሳሳይ ድርሻ የተሸፈነው በውሃ ነው። ውሃ ከሰው ልጅም ሆነ ከማንኛውም የተፈጥሮ ውጤት ጋር ትልቅ ቁርኝነት አለው። እኔ እንኳን ለዛሬ ስለ ውሃ ምንነት እና ጥቅም ሳይሆን ላካፍላችሁ የፈለግኩት፤ አንድ የጃፓን ተመራማሪ በውሃ ላይ ያደረጉትን ምርምር እና ምናልባትም ለራሳችን ያለንን አመለካከት እስከወዲያኛው ሊቀይር የሚችለውን ግኝታቸውን ነው።...

አዋቂነት….. ሞኝነት?

ልጅ እያለን፤ ለደስታ ያለን አመለካከት የተለየ ነበር። ለመሳቅ ምክንያት አያሻንም ነበር፤ ለመደሰት ልጅ ከመሆናችን የዘለለ መስፈርት አልነበረንም ነበር፤ ደስታ ግብ ሳይሆን ከማንነታችን ጋር፤ ከልጅነታችን ጋር አብሮ የተዋሃደ የተፈጥሮ ጸጋ ነበር። እድሜ ሲጨምር እና ማደግ የሚሉት ፈሊጥ ሲመጣ  እኛ ለደስታ ያለን አመለካከት ተለወጠ (ነገር ግን ደስታ ምንነቷ የተለወጠ ነው የሚመስለን)  ። አንድ ጸሃፊ የልጅነትን መልካም...

እራስህን ሆነህ ፍካ……

አልፎ አልፎ ከምሰማቸው ተራናጋሪዎች ወይም አስተማሪዎች ማለት እችላለው፤ ሳድጉሩ የተባለው ህንዳዊው  ዮጊ ( sadhguru) አንዱ ነው። ዛሬ ደስ የሚል መልዕክት ሰማሁኝ እና ላካፍላችሁ ፈለግኩኝ። በቅድሚያ እራስን ስለመለወጥ ያለን አስተሳሰብ ምንድን ነው? እራሳችንን መቀየር አለብን ስንልስ ምን መለወጥ እንደምንፈልግ እናውቃለን? መለወጥ የምሻውስ ሰዎች እንዲወዱን እና እንዲቀበሉን ብለን ነው ወይስ አሁን ያለንበት ህይወት...

ምንጩን ትተን….ሌላ ጉድጓድ ቁፈራ

ብዙዎቻችን፤ በፍቅር ግንኙነታችንም ሆነ በተለያዩ ግንኙነቶቻችን ውስጥ፤ ፍቅርን ያለቦታው  እናስሰዋለን፤ አለመፍለቅቂያው እንፈልገዋለን። ለዚህም ነው ፍቅር ደብዛው የጠፋ የሚመስለው። አንድ የውጪ ሃገር መምህር ይህንን ደስ በሚል ቋንቋ እንዲህ ገልጸውታል “በአህያው ጀርባ ላይ ሆነው አህያውን እንደመፈለግ ማለት ነው” ሲሉ። ፍቅርን የምንፈልግ ሰውች ልክ አህያው ላይ ተቀምጦ አህያው ወዴት ነው ብሎ...

ዛሬ ደግሞ እስቲ እኔ ልውለድሽ

  እንዴት አድርጌ እንደማርግዝዥ ባላውቅም፤ ልወልድሽ አስቤያለው። ስቃይሽ አልገባኝ ቢል መስዋትነትሽን ባልረዳው፤ ውለታሽን መክፈል ቢያቅተኝ፤ ጥልቅ የሆነው እናትነትሽን ለመመርመር ቢከብደኝ፤ በተራዬ ልወልድሽ ወሰንኩኝ።  ምን ላድርግ ፍቅርሽን እኮ የሰው ህሊና ሊመረምረው ፤ ውለታሽን የሰው ልብ ሊሸከመው  አይችልም። እንኳን ሰው እኔ የስጋሽ ክፋይ አልተረዳሁትም…….እናም ልወልድሽ ወሰንኩኝ።...