“Be the change you want to see in the world.”

አሻራዬ መነቃቂያ ገፅ

“Be the change you want to see in the world.”

አሻራዬ መነቃቂያ ገፅ

ስሩ ውሃ ካልጠጣ…..የጠወለገውን ቅጠል ውሃ  ብናርሰው ምን ሊበጀው?

ይህን ታሪክ የሰማሁኝ እለት፤ እራሴን በተለየ አይን ተመለከትኩት። ወደኋላ ተመልሼ ህይወቴን ቃኘሁት፤ ምናልባት የብዙዎቻችን ኑሮ ይገልጽ ይሆናል በማለት ታሪኩን እንዲህ አሰናድቼዋለው። ሰውየው በቤቱ አንድ ትልቅ ዛፍ ነበረው አሉ፤ ይህ ዛፍ ህልውናው እንደትንጠለጠለበት ሁላ በእጅጉ ይንከባከበው ነበር። በቀን በቀን፤ ሲመሽም ሲነጋም ወደ ዛፉ እየሄደ ምርጥ ጊዜ ያሳልፋል። ከእለታት አንድ ቀን ግን፤ ይህን ግዙፍ ዛፍ ትክ ብሎ...

“የሰው ልጅ  ከባዱን ጥላቻን ከተማረ፤  ቀላሉን ፍቅርንም መማር ይችላል….. “

መቼም አለማችን አሁን ያለችበት ደረጃ ከዚህ በፊት ደርሳ አታውቅም። በስልጣኔ በእውቀት እና በምርምር፤ ይህን ዘመን የሚያክለው ማን አለና?  በተቃራኒው ደግሞ ፍቅር እና ሰላም ቦታቸውን እየለቀቁ በሁላችንም ህይወት ውስጥ ባዶ ስፍራ እያስቅሩ ሲሸሹ ይታያል። አለም የጠበበችን ያህል፤ ጦርነቱ እና ስቃዩ አንዳንዴ ዝም ብሎ ለሚያስተውለው ሰው ተስፋ ያስቆጥራል። ጥላቻን እንዲህ ከየት ለመድነው ያሰኛል፤ ሁላችንም የምድር እንግዶች...

ህይወታችን በራሳችን ቁጥጥር ስር ለማድረግ የሚረዱን መንገዶች-ክፍል ፫

ለማን ነው የምንኖረው?…..መልስ የሚያስፈልገው ጥያቄ!!! በትንሹ እበድ- አንዳንዴ በእብድ ሰው ቀንታችሁ አታውቁም? ያሰበውን ተናግሮ፤ የፈለገውን አድርጎ፤ ስለሰው ሳይጨነቅ፤ በይሉንታ ሳይታሰር፤ ከሰው በላይ ነጻነት አግኝቶ ሲኖር ትንሽ አይገርምም?  እንበድ እያልኩኝ ሳይሆን የኛ ጤንነት ትንሽ አልበዛም ትላላቹ? ስለሰው ኖርን፤ ስለሰው አስበን፤ በይሉኝታ የማንፍልገውን ህይወት መርጠን፤ እስከመቼ እንኖራለን?...

ህይወታችንን በራሳችን ቁጥጥር ስር ለማድረግ የሚረዱን መንገዶች-ክፍል ፪

ለራሳችን ምን ያህል ጊዜ እንሰጣለን? ኑሮዋችን ከጊዜው ጋር ይበልጥ እሩጫ እየሆነ መሄዱ እርግጥ ነው። አብዝተን ስራ እንሰራ ይሆናል፤ ከቤተሰብ ጋር ጊዜ ማሳለፋችን ግድ ነው፤ ጓደኝነትም የራሱን ጊዜ መውሰዱ አይቀርም። ግን በዚህ መሃል፤ ከሁሉም በላይ አስቀድመን ጊዜ ልንሰጠው የሚገባውን ሰው የረሳነው አይምስላችሁም? ይህ ሰው የገዛ እራሳችን ነው። ለራሳችን ምን ያህል ጊዜ እንሰጥ ይሆን? ለራስ ጊዜ መስጠት ማለት፤...

አንድ ሺህ መስታወቶች

ያንተ ተጽዕኖ እስከ ምን ድረስ ይመስልሃል? አስተሳሰብህ ኑሮህ ላይ፤ ጤንነትህ ላይ፤ ከሰዎች ጋር ያለህ ግንኙነት ላይ፤ ሃብትህም ላይ፤ ምን ያህል ድርሻ አለው ብለህ ትገምታለህ ?ብዙዏችን እራሳችን (በተለይም አስተሳሰባችን) የራሳችን ህይወት ላይ ያለውን ትልቅ ተጽዕኖ አናውቅም። ጥቂቶች ግን ይህንን ሚስጥር ስለሚያውቁ፤ አስተሳሰባቸውን በመሞረድ አይምሮዋቸው ከተለመደው በላይ እንዲያገለግላቸው ሲያደርጉ እና ህይወታቸው እንደ...