የ“ጥቅም የለሽነት” ስሜት

Posted on Posted in አፈንጋጭ ሃሳቦች

የ“ጥቅም የለሽነት”ን ስሜት ሁላችንንም በአንድ ወቅት ተዋውቀነዋል። በተለያየ መልኩ ድል ብንነሳውም እንኳን ደጋግሞ ይጎበኘናል። የሚያስገርመው ታላቅ የሚባሉ እና ብዙ ስራ የሰሩ ሰዎች እንኳን ይህ የ”ጥቅም የሌሽነት” ስሜት እና የከንቱነት ስሜት ሽው እንደሚላቸው ሲናገሩ ይሰማል። እናም እንዲህ የሚሰማህ ከሆነ ብቻህን አይደለህም……

ስለ ጥቅም የሚጨነቀው ሰው ብቻ ነው። ዛፍ ጠቃሚነቱ አያስጨንቀውም፤ የዛፍን ሺህ ጥቅም አስባችሁ ድረሱበት፤ ፀሃይ ጠቃሚነቷ አያሳስባትም፤ጨረቃም እንደዛው፤ ወንዝ ከንቱ ነኝ ብሎ ፈፅሞ በሃሳብ አይሞገትም። ለምን? እራሳቸውን ስለሆኑ……..ጥቅም ለመስጠት እኮ እራስን መሆን እና ተፈጥሮን አለመልቀቅ ይቀድማል።

እኛ ሰዎች ተፈጥሮዋዊነታችንን ስለለቀቅን፤ አኗኗራችንን ውስብስብ አደረግነው እንጂ……..ሰከን ብለን ብናስበው ከተፈጥሮ ጋር መልሰን ብንዋሃድ ሰላማችንን ማስመለስ እንችላለን።
(የፓውሎ ኮዌሎን መፅሃፍ ሳነብ ካገኘሁት ሃሳብ በመነሳት የሞነጫጨርኳት ናት)dont say you dont have purpose

Do you have any comments?