“Be the change you want to see in the world.”

አሻራዬ መነቃቂያ ገፅ

“Be the change you want to see in the world.”

አሻራዬ መነቃቂያ ገፅ

በምክንያት አትታሰር!!!

ለውድቅታችን ብዙ ምክንያቶችን መስጥት ለምድናል። ወደ ሁላ ለቀረንበት፤ የፈለግነውን ሳይሆን ያልፍለግነውን ለመሆናችን፤ ምክንያቱን ብንጠይቅ፤ እጅግ ብዙ ነገሮችን ለመደርደር እንችላለን። ግን ሁሌም ምክንያቶች በኖሩን ቁጥር፤ ውድቀታችንን በጸጋ ለመቀበል ዝግጁ ነን ማለት ነው ፤ እንደዛ ማለት ብቻም ሳይሆን ለወደፊቱ ውድቀታችንም ዝግጁ ያደርገናል ህልም ካለህ እና ህልምህ ለህይውትህ ትልቅ ትርጉም ካለው፤ ከባዶ ማንነት...

ጥበብ መውለድ ያቆመችው እሷ መካን ሆና ሳይሆን ትውልዱ መክኖ ነው!

በመጀመሪያ ይህን ፅሁፍ ለመፃፍ ያነሳሳኝ፤ በማህበራዊው ገጽም ላይ ሆነ በተለያዩ ቦታዎች የሰውን ስራ እና ፈጠራ እንደራሳቸው አድርገው የሚያቀርቡ ሰዎችን በማየቴ እና በመታዘቤ ነው። በዚህ ዘመን ስነፅሁፍን እና ሌሎች የፈጠራ ስራዎችን አስመልክቶ የሚባል ነገር አለ፤ አዲስ የጥበብ ስራ ጠፍቷል “ጥብብ መክናለች” እያሉ ሲያዝኑ ሰምታችሁ ይሆናል። እኔ ግን ጥበብ አልመከነችም እኛ ነን መካኖቹ ባይ ነኝ ። አዲስ ነገር መስማት፤...

የ“ጥቅም የለሽነት” ስሜት

የ“ጥቅም የለሽነት”ን ስሜት ሁላችንንም በአንድ ወቅት ተዋውቀነዋል። በተለያየ መልኩ ድል ብንነሳውም እንኳን ደጋግሞ ይጎበኘናል። የሚያስገርመው ታላቅ የሚባሉ እና ብዙ ስራ የሰሩ ሰዎች እንኳን ይህ የ”ጥቅም የሌሽነት” ስሜት እና የከንቱነት ስሜት ሽው እንደሚላቸው ሲናገሩ ይሰማል። እናም እንዲህ የሚሰማህ ከሆነ ብቻህን አይደለህም…… ስለ ጥቅም የሚጨነቀው ሰው ብቻ ነው። ዛፍ ጠቃሚነቱ አያስጨንቀውም፤ የዛፍን ሺህ ጥቅም...

የፈቃድ ባርነት

የባርነትን ታሪክ ለሚያውቀው፤ ቢደበዝዝ እንኳን የማይጠፋ ቁስል ነው። እኔ እንኳን በዚህ ፅሁፍ ለማንሳት የፈለግኩት የጥቁሮችን የባርነት ታሪክ ሳይሆን፤ እኔ እና እናንተ ያለንበትን የፈቃድ ባርነት ልብ እንድንለው ስለፈለግኩኝ ነው። የኛ ባርነት፤ ጥቁሮቹ ላይ እንደተፈፀመው ያለፈቃድ የሆነ ግፍ ሳይሆን፤ በገዛ ፈቃዳችን የተዘፈቅንበት ባርነት ነው። ጨቋኞቻችን ቢለያዩም እንኳን፤ አብዛኛዎቻችን የፈቃድ ባሪያዎች ሆነን፤...

እኔ እና “እኔ”

ሳልቀጥረው ነው የመጣው። ሳይቀጠር የሚመጣ እንግዳ ችር ወሬ ይዞ የሚመጣ አይመስለኝም። ለሁሉም ነገር ተዘጋጅቼ መጠበቅን ልምዴ አድርጌዋለው። እናም “እኔ” ዛሬ ሳልጠብቀው፤ ሳልቀጥረው፤ ሳይነግረኝ ብቅ አለ። “እኔ” ሳይታሰብ ፊቴ ቆመ። ምን ዜና ይዞልኝ እንደመጣ ከፊቱ ለመገመት አልቻልኩም። ፊቱ ላይ ምንም አይነት ሰሜት አይታይም፤ ደስታም ሆነ ሃዘን አይነበብም። ባዶ ስሜት….ባዶ ገፅታ….ባዶ መንፈስ። ሁሌም እንደምሸሸው...