“Be the change you want to see in the world.”

አሻራዬ መነቃቂያ ገፅ

“Be the change you want to see in the world.”

አሻራዬ መነቃቂያ ገፅ

ሶሰቱ ማጣሪያዎች (Socrates’ Triple Filter Test)

በጥንታዊቷ ግሪክ ውስጥ ሶቅራጠስ ከሰው ሁሉ የተለየ እውቀት እንዳለው ይነገር ነበር። ፍልስፍናው እና እውቀቱ በዘመኑ ከነበሩት ሰዎች እንዲለይ አድርጎታል ። ከእለታት አንድ ቀን አንድ ለወሬ የቸኮለ ሰው ሶቅራጠስን በመንገድ ያገኘውና እንዲህ ሲል ይነግረዋል። “ሶቅራጠስ……ስለ ጓደኛህ የሰማሁትን ነገር አውቀሃል?” ብሎ ወሬውን ሊቀጥል ሲል “አንዴ አቁም” አለው ሶቅራጠስ ቀጥሎም “አንድ ፈተና አለኝ…….”ሶስቱ ማጣሪያዎች”...

ደስተኛ ሰው ማን ነው?

መጠየቅ የማይሰለቸው አይመሮዬ ሁሌም መልሶ መላልሶ ከሚጠይቃቸው ጥያቄዎች ውስጥ አንደኛው ……. “ደስተኛ መሆን ምን ማለት ?” የሚለው ዋነኛው ነው። አንድ ማን እንደተናገረው የማላስታውሰው አባባል ትዝ አለኝና ይኸው አሰፈርኩት “በልጅነቴ ፈተና ስፈተን ምን መሆን ትፈልጋለህ ተብዬ ስጠየቅ “ደስተኛ መሆን” የሚል መልስ ሰጠው…..ፈተናውን የሚያርመው አስተማሪ “ጥያቄው አልገባህም” ብሎ ተቆጣኝ…..እኔ የማውቀው ግን አስተማሪው...

ከዶሮ መካከል የወደቀ ወፍ አትሁን

ከእለታት አንድ ቀን ምድር የመሬት መንቀጥቀጥ ደረሰባት፤ መንቀጠቀጡ መሬት ላይ ያለውን ሁሉ ማነቃነቁ አይቀርምና ሁሉም ተናወጠ። በወቅቱ ከዛፍ ላይ አንድ የወፍ ጎጆ ነበረች፤ ይህች የወፍ ጎጆ በውስጧ እንቁላሎችን ይዛ ነበር። መሬቱ ሲንቀጠቀጥ ግን እንቁላሎቹን ይዛ ከነበረችው ጎጆ ውስጥ አንዱ እንቁላል ከዶሮዎች መንደር ወደቀ። ዶሮዎቹ እንቁላሉን እንደ እራሳቸው እንቁላል ተንከባክበውና ታቅፈው እንዲፈለፈል አደረጉት። ወፉ...

ወደ አላማህ እየተጓዝክ ከሆነ የተመልካቹን ጩኸት አትስማ

ብቅ ባልኩኝ ቁጥር የሚኮረኩሙኝ ሲበዙ……በእኔ ቅድሚያ ማመን ያለበት ማነው? እያልኩኝ ማሰብ ጀመርኩኝ፤ እኔ ወይስ ሌሎች ሰዎች? ከልጅነት እስከ እውቀቴ ድረስ አንድ ነገር ለመስራት ስነሳ “አዪ…..ይህማ የማይሆን ነገር ነው”፤ “ አይሳካም”፤ “ሁሉም ሰው ሞክሮት አልተቻለም” የሚሉ ኮርኳሚ ንግግሮችን እስኪሰለቸኝ ሰምነቻለው። ሰምቻለውም ብቻም ሳይሆን ተቀብያቸው እግር እና እጆቼን እንደካቴና አስረዉኝ ኖረዋል። ሁሉም በክፋት...

ያልተሄደበት ጎዳና

  ህይወትን ሲኖሩዋት ደስ የምትለው ለመኖር ምክንያት ሲኖረን ነው። ለመኖር ምከንያት እና አላማ የሌለው ሰው እንዴት ነገው ያጓጓዋል? እንዴትስ ወደፊት ለመራመድ ብርታት እና ጉልበት ይገኛል? ህይወት ያቀረበችልንን ብቻ የምንቀበል ከሆነና የምንፈልገውን የማንጠይቅ ከሆነ የምድር ሸክም ከመሆን የዘለለ ኑሮዋችን ምን ትርጉም ይኖረዋል? ሰው የተጓዘበትን መንገድ ተከትሎ የሚጓዝ ፤ ለዘመናት የተደቀደቀው ጎዳና ላይ...