መነቃቂያ

 በዚህ ገጽ የደከሙ መንፈሶችን፤ የጠወለጉ ህይወቶችን፤ ተሰፋ የቆረጡ ልቦችን የሚያክሙ እና የሚያለመልሙ ፅሁፎች የሚቀርቡበት ነው። ሰው እንዳስተሳሰቡ ይኖራልና ፤ ኑሮዋችን እንዳሰብነው ካልሆነ አስተሳሰባችንን መፈተሹ መልካም ነው። ለዚህም ነው የማነቃቂያ ፅሁፎችን ለመፃፍ እና ለአንባቢያን ለማስተላለፍ የወደድኩት።
ሃሳብ ሲገባዎ፤ ጭንቀት ሲፈታተንዎ ወደዚህ አምድ ጎራ ይበሉ እና መንፈስዎትን ያድሱ። የተሻለች ኢትዮጵያን ለመፍጠር ካሰብን በአስተሳሰብ ጠንካራ ትውልድ መጀመሪያ መፍጠር እንዳለብን መዘንጋት የለብንም። በዚህ ገፅ የሚቀርቡ ሃሳቦች በሙሉ እራሳችንን እንድንመለከት እና እንድንፈትሽ የሚያደርጉ ናቸው። ህይወታችንን መለወጥ ከፈለግን በመጀመሪያ አስተሳሰባችንን መቀየር ይገባናል።
በዚህ አምድ ስር የሚሰፍሩ ፅሁፎችን ለማንበብ…..ከተቻች ያለውን “መነቃቂያ” የሚለውን ሊንክ በመጫን ወደፊት እና ወደኋላ በማድረግ ማንበብ ይቻላል።
መልካም ንባብ
ሚስጥረ አደራው